ከአቶ አባይ ጸሃየ አንደበት 5 ቁም ነገሮች

ታሕሳስ 02 2011(ድወት) አቶ ኣባይ ፀሃየ ለቢቢሲ የተናገሩዋቸው አምስት ጉዳዮች:-

1.ዲሞክራሲያዊ ነን በሚሉ ሃገራት አንድ ፓርቲና አንድ ግለሰብ ከሠራዊት ወይም ከድህንነት ኃላፊነት ሲነሳ ስንት ኩርፍያና ግርግር ይፈጠራል። ህወሓት ግን አካሄዱ ላይ ይስተካከል ብሎ አስተያየት ሰጥቷል፤ ነገር ግን ተግባራዊ አድርጎታል። የቱ ጋር ነው ለውጡን የተቃወመው?

2.ውጭ የነበሩት ተቃዋሚ ኃይሎች በአጭር ጊዜ እንዲገቡ መደረጉ ህወሓትም የትግራይ ሕዝብም አድንቋል። አብዛኛው በይቅርታና በፍቅር መንፈስ፤ አንድነትን በመፍጠርና ዲሞክራሲን በማስፋት መንፈስ ነው የመጣው። ጥቂቶቹ ግን ከእነ ቂም በቀላቸው ነው ያሉት።

3.ለውጥ ሲባል እናጨብጭብ ማለት አይደለም። ጥሩ ፈር ይዞ የሄደውን እናጨብጭብለት። ዳር እናድርሰው። በስመ ለውጥ ያልሆነ ነገር ተደባልቆ የሚፈፀም ሌላ ጤነኛ ያልሆነ ነገር ካለ ደግሞ .. ማረም ለውጡን ከጉድለት ማፅዳት እንጂ መቃወም አይደለም!

4. ሃገሪቱ ለገባችበት ችግር፣ .. ዋናው ተጠያቂ ኢህአዴግ የእራሱ ሥራ አስፈፃሚ ነው ብሎ ነው የገመገመው። ህወሓት ነው ብሎ አልገመገመም።

5.አንድን ሕዝብ ማግለልና ማስከፋት የጀመረ መንግሥት ሌላውንም ማስከፋቱና ማግለሉ አይቀርም። የጊዜ ጉዳይ ነው::